Daily Weather Report 26 February 14

Weather Summary for previous day

Feb. 13, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደሌ እና ብሉ ሆራ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy skies over the southern, southwestern, western, and central parts of our country. Along with this, light to moderate rain was recorded in Bedelle and Bule Hora. Elsewhere, the daytime maximum temperature recorded 38.0°C in Gode.

Weather Forecast for next day

Feb. 15, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የጅማ ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow there will be cloudy skies over the southern, south‑western, western and central parts of the country. In addition, light to moderate rain is expected in parts of Oromia Region Jima, Ilubabor and Buno Bedelle zones; Southern Ethiopia Region, Gofa zone; South West Ethiopia Region Bench Sheko, Sheka, Kefa and West Omo zones; and Gambela Majang zone. Meanwhile, forecast indicate that daytime Maximum temperatures exceeding 35°C in Gambela, Funyido, Lare, Abobo, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridahar and Gode.