Daily Weather Report 26 February 13

Weather Summary for previous day

Feb. 12, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጎሬ፣ ጋቲራ፣ ሶኮሩ፣ ቦሬ፣ ባሌሮቤ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ምዕራብ አባያ፣ ኮንሶ፣ ጊዶሌ፣ ሆሳዕና እና እምድብር ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ እንዳባጉና፣ መተሐራ፣ ምዕራብ አባያ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed over the southern, southwestern, western, and central parts of the country. As a result, light to moderate rainfall was recorded in Gore, Gatira, Sokoru, Bore, Bale Robe, Masha, Tercha, Mirab Abaya, Konso, Gidole, Hosanna, and Emdibir. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Village 11, Mayhansa, Yechila, Endabuguna, Metehara, Mirab Abaya, and Gode, the daily maximum temperature ranged from 35 to 41.5°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 14, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የጅማ እና ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ባስኬቶ ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over the southern, southwestern, and western parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall is anticipated in Jimma and Guji zones of the Oromia Region; Gofa, Gedeo, South Omo, and Basketo zones of the South Ethiopia Region; and Bench Sheko, Sheka, Kefa, and West Omo zones of the Southwestern Ethiopia Region. On the other hand, the forecast indicates that the maximum daily temperature will exceed 35°C in Gambella, Fugnido, Lare, Abobo, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar, and Gode.