Daily Weather Report 26 February 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በሻምቡ፣ ባህርዳር፣ ጎሬ፣ ማሻ፣ ኢጃጂ፣ ዲላ፣ ኩሚ፣ ይርጋለም፣ ሐረር፣ አቃቂ እና አዲስ አበባ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ መንደር11፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጨዋቃ፣ ሳውላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ብላቴ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northeast, west, south, central and southwest parts of the country. As a result, light rain was experienced in Shambu, Bahir Dar, Gore, Masha, Ejaji, Dilla, Kumi, Yirgalem, Harar, Akaki and Addis Ababa. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Lare, Village 11, Mayhansa, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Metahara, Chewaka, Saula, Mirab Abaya, Bilate, Kebridehar and Gode, the highest daily temperatures were recorded at 35-41.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂና ጉጂ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጌዴኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች ፤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ34°C በላይ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southwest, south and west of the country. In connection with this, the West Guji and Guji and Jimma zones of the Oromia region; The Gofa, Gedeo and Basketo zones of the Southern Ethiopian Region; and the Bench Sheko and Kefa zones of the Southwestern Ethiopian Region; will receive light to moderate rainfall. On the other hand, numerical forecast indicates that the maximum daily temperature will be recorded above 34°C in Gambella, Fundo, Lare, Abobo, Sherkole, Kumruk, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode.