Daily Weather Report 26 February 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በላሊበላ፣ ጋሸና፣ ፉኝዶ፣ ቴፒ እና ሐዋሳ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ መንደር11፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ እንዳባጉና፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northeast, west, south, and southwest parts of the country. As a result, light rain was experienced in Lalibela, Gashena, Fugendo, Tepi, and Hawassa. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Lare, Village 11, Yecla, Mayhansa, Endabaguna, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Metahara, Kebridehar and Gode, the highest daily temperatures were recorded at 35-39.6°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ከምባታ ዞኖች ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ መንደር11፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, southwest, south, west and central parts of the country. In connection with this, the West Shewa, West Arsi and Arsi, Horo Gudru, East and West Wellega and Jimma zones of the Oromia region; The Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Sidama Region zones; the Hadiya and Kembata zones of the Central Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, West Omo and Kefa zones of the Southwestern Ethiopian Region; and the Anuak, Itang and Majang zones of the Gambella Region will receive light to moderate rainfall. On the other hand, forecast indicates that the maximum daily temperature will be recorded above 35°C in Gambella, Fugendo, Lare, Abobo, Moro 11, Metema, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode.