Daily Weather Report 26 February 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በምስራቅ ጎጃም፣ ጋምቤላ፣ ኢሉባቦር፣ ፣ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ጌዴኦ እና በሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ መንደር11፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ እንዳባጉና፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-42.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northwest, west, south and southwest parts of the country. As a result, light rains were experienced in the East Gojam, Gambella, Ilubabor, West Omo, Dauro, Gedeo and Sidama regional zones. On the other hand, the highest daily temperatures in Gambella, Fugendo, Kidame Gebeya, Village 11, Yecla, Mayhansa, Endabaguna, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode were recorded at 35-42.5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፤ በደቡብ ምስራቅ እና በጋምቤላ ክልል አከባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, southwest, south, west and central parts of the country. In connection with this, the West Shewa, West Arsi, Horo Gudru, East Wellega and Jimma zones of the Oromia region; the Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones of the Southern Ethiopia region; the Sidama region zones; The Bench Sheko, Sheka and Kefa zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Anuak and Majang zones of the Gambella Region; and the East and West Gojam, South Gondar and South Wollo zones of the Amhara Region will receive light to moderate rainfall. On the other hand, forecast data indicates that the maximum daily temperature will exceed 35°C in the northwest, southeast, and Gambella regions.