Daily Weather Report 26 February 08

Weather Summary for previous day

Feb. 7, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በሰሜን ሸዋ፣ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the western, southern, southwestern, and central parts of the country. As a result, the North Shewa, Arsi, Borena, Gurage, and Silte zones received light rain. On the other hand, the eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy weather, with the daily minimum temperature recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Feb. 9, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፤ በደቡብ ምስራቅ እና በጋምቤላ ክልል አከባቢዎች ቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, southwest, northeast, south, west and central parts of the country. In connection with this, the Guji and West Guji, Bale, West, North and Southwest Shewa, West Arsi and Arsi and Jimma zones of the Oromia region; Addis Ababa; From the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gofa, Gamo, South Omo, Basketo and Gedeo zones; Sidama Region zones; From the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; From the Central Ethiopian Region, Gurage, Silte, East Gurage, Kebena Special Zone, Hadiya, Mareko Special Zone, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; The Anuak and Majang zones of Gambella region and the East Gojam, North Shewa and South Wollo zones of Amhara region will experience light to moderate rainfall at isolated places. On the other hand, the forecast indicates that the maximum temperature will exceed 35°C in the northwest, southeast and Gambella regions.