Daily Weather Report 26 February 07

Weather Summary for previous day

Feb. 6, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ሀድያ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the northeast, northwest, west, southwest, and central parts of the country. Accordingly, North and South Wollo, East and West Gojjam, North Shoa, West Wellega, Southwest Shewa, Guji and West Guji, Hadia, Dauro, Wolaita, and Sidama region received light rainfall. On the other hand, dry, sunny, and windy weather was observed in the northeast and eastern parts of the country, with temperatures dropping below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Feb. 8, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ደቡብ ወሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the western, southwestern, northeastern, southern and central parts of the country. In connection with this, the zones of Guji and West Guji, Bale, Southwest Shewa, West Arsi and Arsi and Jimma of the Oromia Region; the zones of Wolaita, Gofa, Gamo, South Omo, Basketo and Gedeo of the Southern Ethiopia Region; the zones of Sidama Region; From the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; from the Central Ethiopian Region, Gurage, Silte, East Gurage, Kebena Special Zone, Hadiya, Mareko Special Zone, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; from the Gambella Region, Anuak and Majang Zones and in the Amhara region, West Gojam, North Shewa, North and South Wollo zones will receive light to moderate rainfall in some areas. On the other hand, the northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather, with forecast indicating that the daily minimum temperature will be below 5°C in some highland areas of the country.