Daily Weather Report 26 February 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዴኦ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, the northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy bega weather, with the daily low temperature recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, there was cloud cover over the northwest, west and southwest parts of the country. As a result, North and South Gondar, East Gojam, North Wollo, Jimma, Buno Bedele, West and East Wollega, Ilubabor, South Omo and Gedeo zones received light rain.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከአማራ ክልል በጥቂት የሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy bega weather; forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5°C in some areas. On the other hand, there will be cloud cover over the southern, southwestern, western and central parts of our country. In connection with this, the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones of the Southern Ethiopia Region; the Sidama Region zones; the Guji and West Guji, Bale, Arsi, Southwest Shewa and East Shewa zones; Gurage, Silte, East Gurage, Hadiya, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region and a few North and South Wollo zones of the Amhara Region will experience light rainfall.