Daily Weather Report 26 February 05

Weather Summary for previous day

Feb. 4, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኮረም፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ፣ ሐሮማያ፣ ጎብየሬ፣ ጅግጅጋ እና ቁሉቢ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በጎሬ፣ ደብረማርቆስ እና ሽንዲ ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather condition was observed over the northern, northeastern, central, and eastern parts of the country. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Korem, Bui, Chelenko, Haromaya, Gobiyere, Jigjiga, and Kulubi. On the other hand, the western and southwestern parts of the country had cloud coverage; consequently, rain was recorded in Gore, Debremarkos, and Shindi.

Weather Forecast for next day

Feb. 6, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ አሌ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ፣ ጅማ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል በጥቂት የምዕራብ ጎጃም እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the northwest, northeast, and east parts of the country will have dry, sunny, and windy Bega weather conditions, with forecast information indicating that the daily minimum temperature will be below 5°C in a few places. In contrast, there will be cloud coverage in the south, southwest, west, and central areas of our country. In this respect, from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, south Omo, Konso, Ale, Gardula, Kore, Basketo and Gedeo zones; the zones of Sidama region; from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Oromia region Guji and west Guji, Bale, west Arsi and Arsi, Jimma, south west Shewa and east Shewa zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Mareko special zone, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak and Majang zones; and a few west Gojjam and south Wollo zones of the Amhara region will receive light rainfall.