Daily Weather Report 26 February 04
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ እና ጅማ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the next day, the western, southwestern, southern, and central parts of the country will have cloud coverage. In line with this, from Oromia region Guji and west Guji, Bale, west Arsi and Jimma zones; from south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, south Omo, Basketo and Gedeo zones; the Sidama region zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Mareko special zone, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak and Majang zones and from Amhara region west Gojjam and south Wollo zones will receive light to moderate rainfall at a few places. On the other hand, the northwest, northeast, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions, with forecast information indicating that the daily minimum temperature will be below 5°C in some of the country's highlands.