Daily Weather Report 26 February 03

Weather Summary for previous day

Feb. 2, 2026

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጎብዬ፣ ኮረም፣ ሐሮማያ፣ ጎብየ፣ ቁሉቢ እና ካራሚሌ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ በታች እና በጨለንቆ ደግሞ -1.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በመካነ ኢየሱስ፣ መርጦለማርያም፣ ወግዲ፣ ደብረማርቆስ፣ ማሻ፣ ጂንካ እና ሆሮዶዮ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the northern, northeastern, central, southern highlands and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy Bega weather. In this regard, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Gobiye, Korem, Haromaya, Gobye, Kulubi and Karamile, and -1.0 degrees Celsius in Chelenko. Conversely, the north western, western, southwestern and southern parts of the country had cloud coverage and rain was recorded in Mekane Yesus, Mertolemariam, Wegdi, Debremarkos, Masha, Jinka and Harodayo.

Weather Forecast for next day

Feb. 4, 2026

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት የምስራቅ አማራ፣ ምስራቅ ኦሮሚያ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የጅማ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም፣ ከምባታ፣ ጌዲኦ፣ ደቡብ ወሎ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the upcoming day, the northwest, northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy Bega weather conditions. Associated with this, numerical forecast information indicates that the minimum temperature of the day will be below 5°C in a few highlands of east Amhara, east Oromia and the east parts of the country. On the other hand, there will be cloud coverage over the western, southwestern and southern parts of our country, and in this respect, Jimma, Guji, West Arsi, Arsi, Southwest Shewa, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem, Kembata, Gedeo, South Wollo zones and Sidama region zones will receive light rain at a few places.