Daily Weather Report 26 February 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በ ሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው በመሆኑም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ላይ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northeast and eastern regions of the country experienced dry, sunny, and windy bega weather, with the daily low temperature recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, there was cloud cover in western and central Oromia, western and eastern Gojam, northern and southern Wollo, northern Shewa, central Ethiopia, southwestern Ethiopia, and Sidama region, resulting in light to moderate rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፤ ጅማ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ጋሞ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy bega weather. In this regard, numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in the southern highlands and eastern parts of the country. On the other hand, there will be cloud cover over the western, central, southern and southwestern parts of the country. Thus, light rain will be experienced over the zones of East Gojjam, North and South Wollo, North Shewa; Jimma, West and North Shewa, Gamo and Sidama regional states.