Daily Weather Report 26 February 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በ ሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው በመሆኑም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ላይ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the northeast and eastern regions of the country experienced dry, sunny, and windy bega weather, with the daily low temperature recorded below 5 degrees Celsius. On the other hand, light to moderate rainfall was recorded in western and central Oromia, eastern Gojam, northern Shewa, central Ethiopia, southwestern Ethiopia and Sidama region.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘም በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፤ ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፤ ጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፤ ወላይታ ሶዶ፣ ጎፋ እና ጋሞ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy bega weather. In this regard, numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in the southern highlands and eastern parts of the country. Therefore, light rain will be experienced in West and East Gojam, North and South Wollo, North Shewa; Jimma, West, South and North Shewa, West Arsi; Gurage, Special Zone, Hadiya; Wolaita Sodo, Gofa and Gamo and Sidama Region zones.