Daily Weather Report 26 April 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከትግራይ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ወሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን ጅማ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ እና ሰቆጣ ከ30.0-42.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መልካ ጀብዱ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ድሬ ደዋ፣ ቀብሪደሃር፣ ጋምቤላ፣ መተሐራ፣ መሆኒ እና ጎዴ ከ35.0-39.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed across the Belg benefiting as well as the western and north parts of the country. As a result, light to moderate rainfall was recorded in the East Borena, Jimma, and East Wollega zones, the West and East Hararghe zones, and Central and Eastern Tigray. Similar rainfall patterns were noted in the Wolayita, Gofa, Gamo, Basketo, and Southeast zones, along with the Gurage Mareko Special Zone, East Gojjam, and North Wollo. Notably, Jimma, Jinka, Sawula, and Sekota experienced heavy rainfall ranging from 30.0 to 42.5 mm. Meanwhile, high daily temperatures between 35.0°C and 39.0°C were registered in Fugnido, Mahansa, Yechila, Melka Jebdu, Ashere, Addis Zemen, Dire Dawa, Kebridahar, Gambella, Metehara, Mehoni, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብና በሰሜን የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ እና የቅልበቲ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ ወለጋ፣ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምስራቅና ደቡብ ትግራይ፣ ዳዉሮ ና ከምባታ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረውም የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover will prevail over the Belg main and secondary rain beneficiary regions, as well as the southern, southwestern, and southeastern parts of the country; additionally, cloud cover will also be present over the western and northern regions of the country. In connection with this, the Southern Ethiopia region zones of Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardula, South Omo, and Gedeo; the Southwest Ethiopia region zones of Bench Sheko, Sheka, Keffa, Konta, West Omo, and Dawuro; the Oromia region zones of Guji and West Guji, Borana and East Borana, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, East and West Hararghe, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Kellem, Horro Guduru and East Wollega, and North, West, Southwest, and East Shewa; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; the Sidama region zones; the Somali region zones of Shebelle, Korahe, Nogob, Erer, Siti, Fafan, Dolo, and Jarar; the Central Ethiopia region zones of Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, the Yem special zone, Kembata, and Tembaro; the Gambella region zones of Majang, Nuer, Agnuak, and Itang; the Tigray region zones of Northwest, Central, East, and Southeast; the Amhara region zones of North, Central, and South Gondar, West and East Gojjam, North and South Wollo, Wag Hemra, the Oromo Nation special zone, and North Shewa; and the Afar region zones of Hari and Kilbet will receive light to moderate rainfall ranging from 1-29 mm. Additionally, East Wollega, Illubabor, Buno Bedelle, Sidama, Wolayta, Sheka, Keffa, East and South Tigray, Dawuro, and Kembata zones will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours; the amount and distribution of this rainfall will be highly beneficial for performing Belg agricultural activities. On the other hand, in Mayhansa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Gode, the maximum temperature will be recorded between 35-40°C.