Daily Weather Report 26 April 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ጉራጌ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ሸካ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን ጅማ እና ቡልቂ ከ30.4-35.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ መተማ፣ ድሬ ደዋ፣ መሆኒ እና ጎዴ ከ35.0-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed over the western and northwestern parts of the country, as well as in areas that typically benefit from the Belg rains. In line with this, light to moderate rainfall was recorded across the Borena and east Borena, Jimma, Southwest and West Shewa West and East Hararghe, Gurage, the Mareko special zone, Sheka, East Gojjam, North Gondar, and North Wollo. Additionally, Jimma and Bulki received heavy rainfall ranging from 30.4 to 35.5 mm. However, high temperatures between 35.0°C and 41.2°C were recorded in Gambella, Fugnido, Mayhanssa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Metema, Dire Dawa, Mehoni, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ሀሪ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣መተከል፣ አሶሳ፣ኢሉባቦር፣ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር እና ጋሞ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover will prevail over the Belg rain beneficiary regions, as well as the western, southwestern, and northwestern parts of Ethiopia. In connection with this, the Oromia region the Guji, West Guji, Borana, Bale, East Bale, Arsi, West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Southwest, East and West Shewa, and West and East Hararghe zones, Harar, Dire Dawa, Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, South Omo, and Konso zones, all zones of Sidama region, the Somali region Siti, Fafan, Nogob, Dolo, Erer, Afder, Korahe, and Shebelle, Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko, Silte, Yem, Hadiya, Halaba, and Kembata Tembaro, Southwest Ethiopia region Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo, the Gambella region Majang, Nuer, Agnuak, and Itang, Benishangul-Gumuz Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao-Komo, and the Awi zone of Afar, the Amhara region, West and East Gojjam, Awi, West, North, Central, and South Gondar, North and South Wollo, the Oromo nation, and North Shewa west and Northwest zones of Tigray will receive light to moderate rainfall ranging from (1-29 mm )is expected across many areas. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is anticipated in Sheka, Metekel, Assosa, Illubabor, Kelem Wollega, West and East Hararghe, Harar, and Gamo. This moisture distribution is expected to be highly beneficial for ongoing Belg season agricultural activities. In contrast, high daily temperatures between 35°C and 40°C will be recorded in Mayhansa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Gode.