Daily Weather Report 26 April 28

Weather Summary for previous day

April 27, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሸካ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ ሐዋሳ፣ ሸበሌ፣ ሰሜን ምዕራብ ፣ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሙንና ደቡብ ወሎ፣ ኮንሶ እና ምዕራብ ኦሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አትናጎ፣ ቢላምቢሎ፣ ዲሜካ፣ ይርጋ ጨፌ፣ ጭራና ሳውላ ከ30.3-57.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ድሬዳዋ፣ ሸርቆሌ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed over the Belg rain beneficiary areas, as well as the western and northern parts of the country. In line with this, light to moderate rainfall was recorded in East Borena, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Kellem, and East Wollega, Gurage, Halaba, Sheka, Wolayta, Gedeo, Hawassa, Shebelle, East Gojjam, North and South Wollo, Konso, and West Omo. Additionally, Atinago, Bilambilo, Dimeka, Yirgachefe, Cira, and Sawula received heavy rainfall ranging from 30.3 to 57.8 mm. However, maximum daily temperatures between 35.2 and 40.8°C were recorded in Mayhansa, Mehoni, Yechila, Ashere, Addis Zaman, Dire Dawa, Sherkole, and Aisha.

Weather Forecast for next day

April 29, 2026

በነገዉ ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ፣በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ሊበንና አፍዴር ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ኑዌር፣ ሸካ፣ ከፋ እና አሶሳ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rain-bearing weather patterns are expected to strengthen across primary Belg rain-benefiting areas, as well as the Northern, Northwestern, Western, and Eastern parts of the country. In line with this, South Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro, South Omo, and Gedeo zones; the Southwest Ethiopia Region Bench Sheko, Sheka, Kaffa, Konta, West Omo, and Dawuro zones; Oromia Region, West Guji, Guji, Bale, East Bale, East and West Hararghe, Arsi, West Arsi, Jimma, Illubabor, Kelem, Horo Guduru, East and West Wollega, and West and Southwest Shewa, Harari and Dire Dawa; the Somali Region Siti, Liben, and Afder zones; the Gambella Region Agnuak, Nuwer, Itang, and Majang zones, the Sidama Region; the Central Ethiopia Region Gurage, Silte, Hadiya, Yem special zone, Kembata, and Tembaro zones; the Benishangul-Gumuz Region Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao Komo zones, the Amhara Region West, North, South, and Central Gondar, Awi, East and West Gojjam, and North Shewa and the Tigray Region Northwestern, Western, Central, and Eastern zones will also see this light to moderate Benishangul-Gumuz Region light to moderate rainfall 1 to 29 mm. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected for the Kelem and West Wollega, Illubabor, Jimma, Nuwer, Sheka, Kaffa, and Assosa zones. However, high-temperature conditions will persist in other parts of the country; maximum daily temperatures between 36°C and 40°C are expected to be recorded in Gambella, Fugnido, Aisha, Kebridahar, Metema, Gewane, Semera, and Elidar.