Daily Weather Report 26 April 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም እና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሸካ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ ሐዋሳ፣ አኙዋክ፣ ሸበሌ፣ ኮንሶ እና ምዕራብ ኦሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአማን፣ ጊዶሌ እና ያዮ ከ31.8-49.3ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ቀብሪደሃር እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed over the areas that benefit from the Belg rains, as well as the western parts of the country. In connection with this, the East Borena, Jimma, Ilu babor, Buno Bedele, Qellem, and East Wollega zones, as well as the West and East Hararghe zones, Harar, Gurage, Halaba, Sheka, Wolayita, Gedeo, Hawassa, Agnuak, Shebelle, Konso, and West Omo, received light to moderate rainfall. Furthermore, heavy rainfall ranging from 31.8 to 49.3 mm was recorded in Aman, Gidolle, and Yayo. On the other hand, maximum daily temperatures between 35.0 and 41.2°C were recorded in Mayhansa, Mehoni, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Kebridahar, and Aisha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን እና አፍዴር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
For the next day, areas that benefit from the Belg rains, as well as the Western and Northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In line with this, many places in the Oromia region Guji, West Guji, Borana, East Borana, Bale, West Arsi, Jimma, Ilu babor, Buno Bedelle, Horro Guduru, Qellam, East and West Wollega, Southwest and West Shewa, and West and East Hararge ; Harar; Dire Dawa; South Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, South Omo, and Konso zones ; all zones of the Sidama region; the Somali region Liban and Afder zones of ; the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the ; Southwest Ethiopia region Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones ; the Gambella region Majang, Nuwer, Agnuak, and Itang zones of ; the Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao-Komo zones of ; the Amhara region West and East Gojjam, Awi, West, North, Central and South Gondar, Waghemra, North and South Wollo zones ; and the East, Central, West, and Northwest zones of the Tigray region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours in the Ilu babor, Sheka, Qellam, and West Wollega zones. Consequently, the anticipated amount and distribution of rainfall will be beneficial for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, the maximum daily temperature will be recorded between 35-40°C in Gambella, Fugnido, Aisha, Kebridahar, Metema, Gewane, Semera, and Elidar