Daily Weather Report 26 April 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ሀድያ፣ ሸካ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቡርጂ፣ ሐዋሳ እና ጋምቤላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was cloudy skies over Belg Benefiting parts of the country. At the same time, rain of light to moderate intensity was recorded in Borena, East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, East and West Wollega, North and East Shewa, West and East Harerge zones; Harar; Hadiya, Sheka, Wolayita, South Omo, Konso, West Omo, Burji, Hawassa and Gambella. Separately, a daytime maximum temperature of 38.8°C was recorded in Fugnido.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ እና ሸካ ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow with cloudy skies over areas that will benefiting Belg and in the west and northwest parts. In line with this from Oromia: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North,south West and West Shoa; Harerge; Dire Dawa. From the Southern Nations, Nationalities and Peoples’ Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones; all zones of Sidama region. From Somali Region: Liben, Afder, and Shebelle zones. From Central Ethiopia: Gurage, Silte, Yeem special zone, Hadiya, and Kembata zones. From Southern Ethiopia Region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones. From Gambela: Majang, Nuwer, Agnuak and Itang zones. From Benishangul-Gumuz: Metekel, Assosa, Kamash and Mao-Komo zones. From Afar: Gabi zone. From Amhara: West and East Gojjam, Awi zone, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo,Waghemra, the Oromia Special Zone, and North Shewa zones. From Tigray: Centeral, west and North West zones. These areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many locations. Additionally, in the Iluababora, Buno Bedelle, Kellem Wollega, and Sheka zones, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. This amount and distribution of rain will be beneficial for carrying out important for Belg season agricultural activities. On the other hand, in Gambella, Fugnido Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar and Gode, daytime maximum temperatures will record about 35–40°C.