Daily Weather Report 26 April 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፣ ድሬዳዋ፤ ጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ፣ ጠምባሮ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ሐዋሳ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በኦንጋ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ካቺሴ፣ መንደር11፣ ግራዋ፣ አርባ ምንጭ እና ጎዴ ከ31.9-88.4ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ መንደር11 እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was cloudy skies over Belg Benefiting and western and northwestern parts of the country. In line with this Borena, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, East Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa; the West and East Hararghe zones; Harar; Dire Dawa; Gurage and East Gurage; Mareko special zone; Silte; Yem special zone; Hadiya; Halaba; Kembata; Tambaro; Sheka; Bench Sheko; West Omo; Wolayita; Basketo; Gedeo; South Omo; Konso; Hawassa; East Gojjam; North Gondar; the Oromo special zone; North Shewa; North and South Wollo; and East Tigray where the rainfall ranged from light to moderate. Meanwhile, in Onga, Nekemte, Shambu, Kachise, Mender 11, Grawa, Arba Minch, and Gode, heavy rainfall was recorded, with amounts between 31.9 and 88.4 mm. On the other hand, daytime maximum temperatures recorded 35.0–38.5°C in Fugnido, Gambella, Mender 11, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምስራቅ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አይሻ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow with cloudy skies over areas that will benefiting Belg and in the west and northwest parts. In line with this from Oromia region in Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Hararge zones; Harari; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Sitti, Fafan, Nogob, Erer, Afder and Shebelle zones; from the Central Ethiopia region Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from the Southwestern Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Asosa, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara region West and East Gojjam, Awi zone, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo and North Shewa zones; and from Tigray region the Eastern zone. The expected rainfall amounts range from light to moderate, about 1–29 mm in many of these locations. Additionally, the Assosa and Mao-Komo zones will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. This amount and distribution of rain will be beneficial for carrying out important for Belg season agricultural activities. On the other hand, daytime maximum temperatures of 35–40°C are expected in Gambela, Funyido, Aisha, Mayhansa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Godé.