Daily Weather Report 26 April 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ፣ ጠምባሮ፣ ሸካ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ አሶሳ፣ ሐዋሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ እና ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በወራቤ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጊኒር፣ ዴጋ፣ ናትሪ፣ ደብረ ሲና እና ሐረር ከ30.6-52.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ አይሻ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.5-39.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was cloudy skies over Belg Benefiting and western and northwestern parts of the country. In line with this Borena, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, North and Southwest Wollega,North,South west and West Shoa; West and East Harerge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Gurage and East Gurage; Mareqo special zone; Silte; Yem special zone; Hadiya; Halaba; Kembata; Tambaro; Sheka; Wolayita; Gedeo; Asosa; Hawassa; West and East Gojjam; West, North and Central Gondar; North Shewa; South Wollo; and East and Southeast Tigray received light to moderate. Heavy rains (30.6–52.7 mm) were recorded at Werabe, Wolayita Sodo, Ginir, Dega, Natri, Debre Sina and Harar. Conversely, Daytime maximum temperatures of 35.5–39.0°C were recorded at Mayhanssa, Mehoni, Funyido, Kebridahar, Metema, Aysha and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጉየጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow with cloudy skies over areas that will benefiting Belg and in the west and northwest parts. In line with this from Oromia: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Harerge zones; Harerge; Dire Dawa. From the Southern Nations, Nationalities and Peoples’ Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region. From Somali Region: Dawa, Liben, Sitti, Fafen, Nogob, Jarar, Dollo, Erer, Afder, Korahe and Shebelle zones. From Central Ethiopia: Gurage and East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones. From Southern Nations, Nationalities and Peoples’ Region (Southwest Ethiopia Peoples’ Region): Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones. From Gambela: Majang, Nuwer, Agnuak and Itang zones. From Benishangul-Gumuz: Metekel, Assosa, Kamash and Mao-Komo zones. From Afar: Gabi zone. From Amhara: West and East Gojjam, Awi zone, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo, the Oromia Special Zone, and North Shewa zones. From Tigray: East and Southeast zones. These areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many locations. Additionally, in the Sheka zone, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. This amount and distribution of rain will be beneficial for carrying out important for Belg season agricultural activities. On the other hand, in Gambella, Mayhansa,Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar and Gode, daytime maximum temperatures will record about 35–40°C.