Daily Weather Report 26 April 23

Weather Summary for previous day

April 22, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉየጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ማጃንግ፣ አኙዋክ፣ አሶሳ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ እና ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ8 ጣቢያዎች ላይ ከ30.6-50.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ጋምቤላ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ መሆኒ፣ ቀብሪደሃር፣ መልካ ጀብዱ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

On the previous day there was cloudy over Belg beneficial areas of country’s, also northwestern part. In addition to that, rainfall was recorded in Guji and western Guji, Borena, western Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Southwest, West, East and North Shewa, West and East Hararghe zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Gurage; Mareqo special zone; Silte; Yem special zone; Sheka; Bench Sheko; Walayita; Gamo; Gofa; Basketo; Gedeo; South Omo; Majang; Angacha; Asosa; East Gojjam; North and Central Gondar; North Shewa; North Wollo and Central; Northwest, East and Southeastern Tigray where received light to moderate rainfall. At eight stations heavy rainfall of 30.6–50.0 MM was observed. On the other hand, in Village11,Gambela,Mayhansa,Yechila,Ashere, Addis Zemen,Chewaka,Metehara, Mehoni, Kebridahar, Melka Jebdu and Gode the daytime maximum temperatures were recorded at 35–39.2°C.

Weather Forecast for next day

April 24, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ እና ኢሉባቦር ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል።

Tomorrow there will be cloudy conditions will prevail over Belg season beneficial areas, also western and northwestern parts of the country. Based on this, many areas will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). These include: from Oromia region Guji and West Guji, Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harari; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Korahe, Gardula and South Omo zones; all zones of Sidama region; from Somali region Sitti, Fafen, Nogob, Jarar, Doolo, Erer, Afder, Korahe and Shebelle zones; from Central Ethiopia region Gurage, Mareko special zone, Silte, Marko special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konso, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamashi and Mao Komo zones; from Afar region Kilbet, Fanti and Hari zones; from Amhara region West and East Gojjam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones; and from Tigray region Central, Northwestern, Northeastern and Southeastern zones. Additionally, in Sheka and Ilubabor zones there may be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. This expected amount and distribution of rain will be beneficial for the implementation of Belg season agricultural activities.