Daily Weather Report 26 April 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ፣ ሀድያ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሐዋሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ8 ጣቢያዎች ላይ ከ30-72.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ጋምቤላ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Cloud cover was observed in the areas of the country that benefited from the belg rains yesterday. In addition, Guji, Borena, Bale and East Bale, Buno Bedele, Ilubabor, West Shewa, East Hararge, Hadiya, Bench Sheko, Hawassa, West and East Gojam, North Gondar, North Shewa, North and South Wollo and East Tigray received light to moderate rainfall; 8 stations received heavy rainfall ranging from 30-72.7 mm. On the other hand, in Mender 11, Gambella, Mayhansa, Yecla, Ashere, Addis Zemen, Saltuka, Dire Dawa, Metahara, Melka Jebdu and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35-39.6°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አውሲ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ ከፋ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል።
Tomorrow, there will be cloud cover in the areas that benefit from the belg rains, as well as in the west and northwest of our country. Accordingly, from the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all zones of the Sidama region; from the Somali region, Dawa, Liben, Siti, Fafen, Nogob, Jarar, Dolo, Korahe and Shebele zones; Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones from the Central Ethiopian Region; The Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones of the Gambella Region; the Metekel, Kamash and Maokomo zones of the Benishangul Gumuz Region; the Awsi, Fanti and Hari zones of the Afar Region; the West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of the Amhara Region; and the Central, North West, East and South East zones of the Tigray Region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places. In addition, the Sheka, Kefa, East and South East Tigray and South Gondar zones will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be important for carrying out belg agricultural activities.