Daily Weather Report 26 April 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ሐረር፣ አሶሳ፣ ሀድያ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጋሞ፣ ሐዋሳ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ሰሜንና ደቡብ ወሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጊዳአያና፣ ሳውላ እና ቡልቂ ላይ ከ30-56.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ አዲስ ዘመን፣ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Cloud cover was observed in the areas of the country that benefited from the belg rains yesterday. Along with this, Guji, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Buno Bedele, Ilubabor, Harar, Asosa, Hadiya, Bench Sheko, Gamo, Hawassa, East Gojam, North and South Wollo received light to moderate rainfall; Gidayana, Saula and Bulki received heavy rainfall of 30-56.6 mm. On the other hand, Fugendo, Mayhansa, Mehoni, Addis Zemen, and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-42.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በዚሁ መሠረትም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ፋፈን፣ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ቆራሄ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አውሲ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና ዋግኸምራ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
Tomorrow Our forecast indicates that favorable weather conditions for rain will continue to prevail in the main areas of the country that receive the belg rains, as well as in the western and northwestern regions of our country. Accordingly, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; ; from the Southern Ethiopian Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso Zones; from all Sidama Region Zones; from the Somali Region: Dawa, Liben, Fafen, Nogob, Jarar, Dolo, Korahe and Erer Zones; from the Central Ethiopian Region: Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; from the Southwestern Ethiopian Region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo Zones; from the Gambella Region: Majang, Nuer, Agnuak and Itang Zones; from the Benishangul Gumuz Region: Metekel, Kamash, Asosa and Maokomo Zones; from the Afar Region: Awsi, Fanti and Hari Zones; From the Amhara region, the West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones and the Central, Northwestern, Eastern and Southeastern zones of Tigray region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. In addition, Jimma, Yem Special Zone, Sheka, Kefa, East and Southeastern Tigray and Waghema zones will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.