Daily Weather Report 26 April 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አሶሳ፣ ሀድያ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጋሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሐዋሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ8 ጣቢያዎች ላይ ከ30-48 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ፓዌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-42.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
yesterday Cloud cover was observed in the areas of the country that benefited from the belg rains. In addition, Guji, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Buno, Bedele, Ilubabor, West, South West and North Shewa, West and East Hararge zones, Dire Dawa, Harar, Asosa, Hadiya, Bench Sheko, Gamo, Wolaita Sodo, Hawassa, West and East Gojam, North Gondar, North Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone and East Tigray received light to moderate rainfall; 30-48 mm of heavy rainfall was recorded at 8 stations. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-42.4°C in Mender 11, Pawe, Mayhansa, Yecla, Gode and Kebridehar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ፣ ሊበን እና ኖጎብ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦኮሞ፣ አሶሳ፣ ካማሺ እና መተከል ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭትም ቀሪ የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ ሸርኮሌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the western and northern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, West, Kelem and East Wellega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Dire Dawa; Harar; Addis Ababa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gedeo, Ale, Kore and Gardula zones; All zones of Sidama Region; Somali Region’s Siti, Dawa, Liben and Nogob Zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dauro Zones; Central Ethiopia Region’s Gurage, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; Gambella Region’s Majang, Nuer, Itang and Agnewak Zones; Amhara Region’s West and East Gojam, North and South Gondar, Waghemra, North and South Wollo Zones; and Benshangul Gumuz Region’s Maokomo, Asosa, Kamashi and Metekel will experience light to moderate (1-29mm) rainfall. In addition, Jimma, Yem Special Zone, Sheka and Kefa Zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours in some areas; the amount and distribution of rainfall will be beneficial for carrying out the remaining belg agricultural activities. On the other hand, in Gambella, Pawe, Sherkole, Mayhansa, Yecla, Elidar, Semera and Gode, the maximum daily temperature will be recorded at 35-40°C.