Daily Weather Report 26 April 19

Weather Summary for previous day

April 18, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌ ሮቤ፣ አርሲ፣ ጎዴ፣ ጎንደር፣ ሞያሌ፣ ቢላቴ፣ ቦሬ፣ ቴፒ፣ ነጌሌ እና ሚኤሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

During the previous day, areas benefiting from the Belg rains, as well as the northwestern parts of the country, experienced cloud cover. Consequently, areas including Bale Robe, Arsi, Gode, Gondar, Moyale, Bilate, Bore, Tepi, Negele, and Meiso received light to moderate rainfall. Meanwhile, Gode recorded a maximum daytime temperature of 38.0°C.

Weather Forecast for next day

April 20, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ ና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ የም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ ሸርኮሌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over areas of the country that are in their main and secondary Belg rainy seasons, as well as in the western and northwestern parts of the country. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is anticipated in several areas, including Guji and West Guji, Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, West, Kellem, Horo Guduru, and East Wollega zones of the Oromia Region; Dire Dawa and Harar; the Gedeo Zone of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; Siti, Dawa, and Fafan zones of the Somali Region; Kafa, Sheka, and Bench Sheko zones of the South West Ethiopia Region; Hadiya, Yem Special Zone, and Kembata zones of the Central Ethiopia Region; Majang, Nuer, Itang, and Agnuak zones of the Gambela Region; Metekel, Kamashi, Assosa, and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; north, central, and south Gondar, Awi, west and east Gojjam zones of the Amhara Region. On the other hand, weather forecasts indicate that in Gambela, Pawe, Sherkole, Mayhansa, Yechila, Aisha, Elidar, Semera, and Gode, the daily maximum temperature is expected to reach between 35°C and 40°C.