Daily Weather Report 26 April 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አዲስ አበባ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በወላይታ ሶዶ፣ ምራብ አባያ፣ ጎሮ በከክሳ እና በቢላቴ ላይ ከ40-44.1 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጎዴ እና መንደር 11 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.0-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, areas that typically benefit from the Belg rains, along with the western parts of the country, were under cloudy condition. As a result, light to moderate rainfall was recorded in areas such as Bale and East Bale, Arsi, Buno Bedele, Illubabor, and the zones of north, east, west, and southwest Shewa, as well as west Hararghe, Dire Dawa, Harari, Addis Ababa, east Gojjam, north Shewa, north and south Wollo, the Oromia special zone, and eastern Tigray. Additionally, some places like Wolayita Sodo, Mirab Abaya, Goro Bekeksa, and Bilate record heavy rainfall, measuring between 40 to 44.1 mm. On the other hands, daily maximum temperatures ranging between 38.0°C and 41.8°C were recorded in Metema, Gode, and Village 11.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ ሸርኮሌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, many parts of the country particularly areas experiencing the primary and secondary Belg rainy seasons, as well as the western parts of the country are expected to have cloud cover. In line with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is forecast over several areas, including Guji and West Guji, Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Kellem, and West Wollega in Oromia Region; Dire Dawa and Harari; Wolayita and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; Siti, Dawa, and Fafan zones of the Somali Region; Kafa, Sheka, and Bench Sheko zones of the Southwest Ethiopia Region; Majang and Agnuak zones of the Gambela Region; Metekel, Kamashi, Assosa, and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; and north Gondar in the Amhara Region. Meanwhile, daily maximum temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected in areas such as Gambela, Pawe, Sherkole, Mahansa, Yechila, Metehara, Aisha, Elidar, Semera, and Gode.