Daily Weather Report 26 April 17

Weather Summary for previous day

April 16, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ፣ ሀድያ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጋሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሐዋሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በየትኖራ፣ አሺ፣ ሞያሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ማርዬ እና መልካ ጀብዱ ላይ ከ30-52 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ፓዌ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. Along with this, Bale and East Bale, Arsi, Buno Bedele, Ilubabor, West, South West and North Shewa, West and East Hararge zones, Dire Dawa, Harar, Addis Ababa, Gambella, Hadiya, Bench Sheko, Gamo, Wolaita Sodo, Hawassa, West and East Gojam, North Gondar, North Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone and Central and South Tigray received light to moderate rainfall; Yetnora, Ashi, Moyale, Wolaita Sodo, Marye and Melka Jebdu received heavy rainfall of 30-52 mm. On the other hand, the highest daily temperatures in Gambella, Fugendo, Pawe, Ashere, Addis Zemen, Mayhansa, Yechila, Gode and Kebridehar were recorded at 35-40.2°C.

Weather Forecast for next day

April 18, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ፣ ሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከአፋር ክልል ሀሪ ዞን ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ ሸርኮሌ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the autumn, as well as over the western and northern parts of our country. In addition, from the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, West, Kelem and East Wellega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Dire Dawa; Harar; Addis Ababa; from the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gedeo, Ale, Kore and Gardula zones; All zones of Sidama Region; Siti, Dawa, Liben and Fafen Zones of Somali Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawro Zones of Southwestern Ethiopia Region; Majang and Agnuak Zones of Gambella Region; West and East Gojam, North and South Gondar, Waghema, North and South Wollo Zones of Amhara Region and Hari Zone of Afar Region will experience light to moderate (1-29mm) rainfall. On the other hand, our forecast indicates that the maximum daily temperature will be recorded at 35-40°C in Gambella, Pawe, Sherkole, Mayhansa, Yecla, Metahara, Aisha, Elidar, Semera and Gode.