Daily Weather Report 26 April 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎችጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጅማ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሀድያ፣ቤንች ሸኮ፣ ጋሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሐዋሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ12 ጣቢያዎች ላይ ከ30-84 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር 11፣ ፓዌ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
yesterday The areas of the country that benefited from the belg rains had heavy cloud cover. Along with this, Bale and East Bale, Jimma, Arsi, Buno Bedele, Ilubabor, West Shewa, West and East Hararge zones, Dire Dawa, Harar, Hadiya, Bench Sheko, Gamo, Wolaita Sodo, Hawassa, West and East Gojam, North Gondar, North Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone and Central and South Tigray received light to moderate rainfall; 30-84 mm of heavy rainfall was recorded at 12 stations. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-40.6°C in Mender 11, Pawe, Addis Zemen, Mayhansa, Yechila, Metahara, Aisha, and Kebridehar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንእና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ እና ምስራቅ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ ባምባሲ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second belg rainy seasons of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem and East Wellega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, South Omo and Gardula zones; All zones of Sidama Region; Somali Region’s Siti, Dawa and Fafen Zones; Central Ethiopia Region’s Gurage, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawro Zones; Gambella Region’s Majang and Agnewak Zones; Amhara Region’s East Gojam, North and South Gondar, Waghema, North and South Wollo Zones; and Central and East Zones of Tigray Region will experience light to moderate (1-29mm) rainfall. On the other hand, our numerical forecast indicates that the maximum daily temperature in Gambella, Pawe, Bambasi, Mayhansa, Yecla, Metahara, Aisha, Elidar, Semera and Gode will be recorded at 35-40°C.