Daily Weather Report 26 April 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሀድያ፣ ሐዋሳ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ፓዌ፣ ባምባሲ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday cloud cover was observed in the areas of the country that benefited from the belg rains. In addition, Bale and East Bale, Arsi, Buno Bedele, Ilubabor, West Shewa, West and East Hararge zones, Dire Dawa, Harar, Hadiya, Hawassa, North and South Wollo and the Oromo National Special Zone received light to moderate rainfall; Mersa and Chewaka received heavy rainfall of 35-40 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Pawe, Bambasi, Mayhansa, Yechila, Metahara, Aisha, Elidar, Semera, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second belg rainy seasons of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East Wellega, West and South West Shewa, West and East Hararge zones; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, South Omo and Gardula zones; All zones of Sidama Region; Somali Region’s Siti and Fafen Zones; Central Ethiopia Region’s Gurage, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawro Zones; Gambella Region’s Majang and Agnewak Zones; Amhara Region’s West and East Gojam, North, Central and South Gondar, Waghema, Oromo Special Zone, North and South Wollo Zones; and Tigray Region’s Central, East and South East Zones will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places. On the other hand, our numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature in Gambella, Pawe, Aisha, Elidar, Semera, Kebridehar and Gode will be recorded at 35-40°C.