Daily Weather Report 26 April 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ጅማ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ዳውሮ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በደብረሲና 38.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ አይሻ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday Cloud cover prevailed in the areas of the country that benefited from the belg rains. Along with this, light to moderate rainfall was recorded in Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, Buno Bedele, Ilubabor, Jimma, West Shewa, Dawro, North and South Wollo and the Oromo National Special Zone; Debre Sina recorded 38.7 mm of heavy rainfall. On the other hand, Gambella, Pawe, Aisha, Elidar, Semera, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።
Tomorrow, there will be cloud cover in the areas that benefit from the belg rains and in the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore and Gardula zones; All zones of Sidama Region; Somali Region’s Siti, Liben and Fafen Zones; Central Ethiopia Region’s Gurage, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dauro Zones; Gambella Region’s Majang, Agnewak and Itang Zones; Afar Region’s Fanti and Hari Zones; Amhara Region’s West and East Gojam, Awi, North, Central and South Gondar, Waghema, Oromo Special Zone, North and South Wollo Zones; and Tigray Region’s Central and Northwestern Zones will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places.