Daily Weather Report 26 April 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ጅማ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ዳውሮ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማጀቴ እና ሰመራ ከ30-34.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፓዌ፣ መተሐራ፣ አዋሽ አርባ፣ ሰመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West Hararge, Buno Bedele, Ilubabor, Jimma, West Shewa, Dawro, North and South Wollo, Oromo National Special Zone and South East Tigray received light to moderate rainfall; Majete and Semera received heavy rainfall of 30-34.2 mm. On the other hand, Gambella, Pawe, Metahara, Awash Arba, Semera and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-39.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ እና ጋርዱላ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg and over the western parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore and Gardula zones; in all zones of Sidama region; ; Somali Region’s Siti and Fafen Erer zones; Central Ethiopia Region’s Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dauro zones; Gambella Region’s Majang, Agnewak and Itang zones; Afar Region’s Kelbeti, Fanti and Hari zones; Amhara Region’s West and East Gojam, Awi, North, Central and South Gondar, Waghema and Oromo National Special Zone, North and South Wollo zones; and Tigray Region’s Central, North West, South and East zones will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.