Daily Weather Report 26 April 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማኦኮሞ ሸካ፣ ፋንቲ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ምስራቅና ሰሜን ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአይደር፣ ሲሪንቃ፣ ገለምሶ፣ አርጆ፣ ቴርጫ እና ደንጌጎ ላይ ከ31.0-67.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጎዴ፣ ማይሃንሳ፣ፓዌ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ የጭላ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the western, north eastern and northwestern regions of the country, which benefited from the autumn rains, had heavy cloud cover. Along with this, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, Buno Bedele, Ilubabor, Horo Guduru, East and West Wellega, North, East, West and South West Shewa, Asossa, Metekel, Maokomo Sheka, Fanti, East Gojam, North Gondar, Waghimra, North and South Wallo and East and North Tigray received light to moderate rainfall; Aider, Sirinka, Gelemso, Arjo, Tercha and Dengego received heavy rainfall ranging from 31.0-67.7 mm. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Gode, Maihansa, Pawe, Elidar, Semera, Yechila and Awash Arba, the maximum daily temperature was recorded at 35.4-40.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሸበሌ፣ ሲቲ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
Tomorrow, there will be strong cloud cover over the main and second rainy seasons of the autumn, as well as over the western, north eastern and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita and Gedeo zones; in all zones of Sidama region; in the Somali region, Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Nogob, Shebele, Siti, Jarar, Dolo and Erer zones; From the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Mem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Kefa, Sheka, Bench Sheko and Dawuro Zones; from the Gambella Region, Majang, Nuer, Agnuak and Itang Zones; from the Benishangul Gumuz Region, Metekel, Kemash, Asossa and Maokomo Zones; from the Amhara Region, West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wallo, Waghimra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa Zones; The Kelbeti, Fanti, Awsi, Hari and Gabi zones of Afar region and the Northwestern, Central, Southern, Southeastern and Eastern zones of Tigray region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many areas. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out autumn agricultural activities.