Daily Weather Report 26 April 08

Weather Summary for previous day

April 7, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ዳውሮ፣ ሸካ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነገሌ እና ማርዬ ላይ ከ30-44.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ማይሃንሳ እና የጭላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-37.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were strong cloud cover in the western parts of the country that benefited from the belg rains. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West Hararge, Buno Bedele, Ilubabor, West and Southwest Shewa, Asosa, Gambella, Dawro, Sheka, East Gojam, Central Gondar, Bahir Dar, North and South Wollo and Northwest Tigray received light to moderate rainfall; Negele and Marye received heavy rainfall of 30-44.5 mm. On the other hand, On the other hand, the highest daily temperatures in Fuengirola, Maihansa and Yechla were recorded at 35-37.5°C.

Weather Forecast for next day

April 9, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በተጨማሪም በምዕራብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ጅማ፣ ሸካ እና ወላይታ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be strong cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all Sidama region zones; in the Somali region, Siti, Fafen, Jarar, Dolo and Erer zones; Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones from the Central Ethiopian Region; The Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones of the Gambella Region; the Metekal, Kamash, Asosa and Maokomo zones of the Benishangul Gumuz Region; the West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of the Amhara Region; and the Central, West, North-West and East zones of the Tigray Region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places. Additionally, our numerical forecast data indicates that heavy rainfall of more than 30 mm will occur in some areas of West Gondar, Awi, West Gojam, Jimma, Sheka, and Wolaita within 24 hours.