Daily Weather Report 26 April 07

Weather Summary for previous day

April 6, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ባህርዳር እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ7 ጣቢያዎች ላይ ከ30-64.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ አዲስ ዘመን፣ አሸሬ፣ መልካ ጀብዱ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were strong cloud cover in the western parts of the country that benefited from the belg rains. Along with this, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West Hararge, Buno Bedele, Ilubabor, Kelem Wellega, Jimma, Gambella, East Gojam, Central Gondar, Bahir Dar and Northwestern Tigray received light to moderate rainfall; 7 stations received heavy rainfall of 30-64.3 mm. On the other hand, Fugendo, Mayhansa, Yecla, Addis Zemen, Ashere, Melka Jebdu and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.0°C.

Weather Forecast for next day

April 8, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በተጨማሪም በአሶሳ፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ሸካ እና ከፋ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all zones of Sidama region; in the Somali region, Siti, Fafen, Jarar and Erer zones; The Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones of the Gambella Region; the Metekel, Kamash, Asosa and Maokomo zones of the Benishangul Gumuz Region; the West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of the Amhara Region; and the Central, West and North West zones of the Tigray Region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. Additionally, Assosa, West and Kelem Wellega, Ilubabor, Buno Bedele, Jimma, Sheka and Kefa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours at some places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.