Daily Weather Report 26 April 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ፣ ሐዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ ጋምቤላ እና ማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቡሬ እና ፉኝዶ ከ30-36.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ መልካ ጀብዱ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
yesterday The areas that benefitted from the belg rains and the western parts of the country had cloud cover. Along with this, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West Hararge, Hawassa, Ilubabor, Horo Guduru, East Wellega, East Gojam, North Wello, Gambella and Central, West and South Tigray received light to moderate rainfall; Bure and Fugendo received heavy rainfall of 30-36.5 mm. On the other hand, Fugendo, Addis Zemen, Mayhansa, Yecla, Melka Jebdu, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በተጨማሪም የምዕራብ ጎንደር፣ ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
Tomorrow, there will be cloud cover over the areas that benefit from the belg rains and the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; In all zones of Sidama Region; Dawa, Fafen, Jarar, Dolo, Nogob and Erer zones of Somali Region; Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones of Southwestern Ethiopia Region; Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones of Gambella Region; Metekel, Kamash, Asosa and Maokomo zones of Benishangul Gumuz Region; West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of Amhara Region And the western and northwestern zones of Tigray region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. In addition, West Gondar, Kelem Wellega, Ilubabor, Sheka, Kefa, West Hararge will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours in some places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.