Daily Weather Report 26 April 05
Weather Summary for previous day
ትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ሲዳማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጋምቤላ፣ ሰሜን ጎንደር እና ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ዋሎ፣ወላይታ እና ኮንሶ ከቀላል ቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቻግኒ 43.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡በሌላ በኩል ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.6 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed across the western, northwestern, southern, and southwestern parts of the country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in Borena, Bale, Arsi, Guji and West Guji, Sidama, Illubabor, Horo Guduru, East Wellega, Gambella, North Gondar, East and West Gojjam, North Wollo, Wolaita, and Konso zones. Additionally, heavy rainfall (43.4 mm) was recorded in Chagni. On the other hand, the daily maximum temperature was recorded in Gode to 36.6 °C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ ትግራይ፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ፣ሆሮ ጉዱሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ባሌ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል ደዋ፣ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ቄለም ወለጋ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ፋፈን እና ሸካ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover in the southern, southwest, and eastern parts of the country which are benefit from the Belg rains, as well as in the western and northwestern parts of the country. In this regard, in western Tigray, northern, southern, and central Gondar, West Gojjam and Awi zones of the Amhara region; from the Oromia region including Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East and West, Horo Guduru and Kelem Wollega, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from southern Ethiopian region Wolaita, Gamo from, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of the Sidama region; from the Somali region, Dawa, City, and Fafen zones; from the central Ethiopian region, Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadia, Halaba, Kembata, and Tembaro zones; from the southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawro, and West Omo zones; from the Gambella region, Majang, Nuwer, Agnuak, and Itang zones; and from the Benishangul-Gumuz region, Metekel, Kamashi, Asossa, and Maokomo zones will have light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. Additionally, in Metekel, Kamashi, Asossa, Maokomo, Ilubabor, West and Kelem Wellega, Nuwer, Agnuak, Bench Sheko, East Hararge, Fafen, and Sheka zones will experience heavy rainfall within 24 hours.