Daily Weather Report 26 April 04

Weather Summary for previous day

April 3, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሲዳማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጋምቤላ፣ ሰሜን ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አዲስ ዘመን፣ መተሐራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover across the West, Northwest, East, Central, South, and Southwestern parts of our country. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Borena, East Bale, Arsi, Guji, West Guji, East Hararge, East and Southwest Shewa, Ilubabor, Horo Guduru, East Wellega, Sidama, Gambella, North Gondar, and East Gojjam. On the other hand, in Gambella, Addis Zemen, Metehara, and Gode, the daily maximum temperature was recorded at 35-41.5°C.

Weather Forecast for next day

April 5, 2026

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ ትግራይ፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ፣ሆሮ ጉዱሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምዕራብና ቄለም ወለጋ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ፣ መተከል፣ አሶሳ እና ሸካ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, Weather events favorable for the formation of rain will continue to intensify in the northwest, west, central, east, south, and southwest areas of the country. In this regard, in western Tigray; northern, southern, and central Gondar, west and east Gojam and Awi zones of Amhara region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, east and west Wellega, southwest and west of Shewa, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena, Gujina and West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in southern Ethiopia Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; Liben and Fafen zones of the Somali region; Gurage zone of the Central Ethiopian region; from southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones; from Gambella region Majang, Nuwer, Anguwak and Itang zones; and Benishangul-Gumuz region Metekel, Kamash, Asosa, and Maokomo zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. Forecast data indicate that in west and Kelem Wellega, Nuwer, Agnuak, Metekel Assosa, and Sheka zones will have heavy rainfall in the next 24 hours.