Daily Weather Report 26 April 03

Weather Summary for previous day

April 2, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ ጋምቤላ እና ማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማሻ፣ አዋሬ እና አሺ ከ30-70.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጋምቤላ፣ አዲስ ዘመን፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ዳሊፋጊ፣ መተሐራ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

yesterday the areas that benefitted from the belg rains and the western parts of the country had cloud cover. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, East Hararge, West, East, South West and North Shewa, Hawassa, Ilubabor, Horo Guduru, East Wellega, East Gojam, North Wello, Gambella and Central, West and South Tigray received light to moderate rainfall; Masha, Aware and Ashi received heavy rainfall of 30-70.2 mm. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-41.5°C in Gambella, Addis Zemen, Gewane, Awash Arba, Dalifage, Metahara, Semera, Elidar and Gode.

Weather Forecast for next day

April 4, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በተጨማሪም በጥቂት የቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ማጃንግ፣ ከፋ እና ሸካ ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

Tomorrow, there will be strong cloud cover over the areas that benefit from the belg rains and the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all zones of Sidama region; in the Somali region, Dawa, Liben, Fafen, Jarar, Dolo and Erer zones, The Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones of the Gambella Region; the Metekel, Kamash, Asosa and Maokomo zones of the Benishangul Gumuz Region; the West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar zones of the Amhara Region and the West and North West zones of the Tigray Region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall at many places. In addition, a few places in Kelem Wellega, Ilubabor, Majang, Kefa and Sheka will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.