Daily Weather Report 26 April 02

Weather Summary for previous day

April 1, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ አሶሳ እና ደቡብ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቡልቂ፣ ገለምሶ እና አሺ ከ30-36.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ አሸሬ፣የጭላ፣ አዲስ ዘመን፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መንደር 11፣ ሰመራ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloud cover in the western and central regions of the country that benefited from the belg rains. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, East, Southwest and North Shewa, Hawassa, Ilubabor, Horo Guduru, East Wellega, East Gojam, North and South Wollo, Asosa and South Tigray; while heavy rainfall of 30-36.4 mm was recorded in Bulki and Ashi. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Gambela, Fugendo, Metema, Ashre, Yechla, Addis Zemen, Gewane, Awash Arba, Village 11, Semera and Elidar.

Weather Forecast for next day

April 3, 2026

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ፋፈን፣ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ቆራሄ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ፤ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በተጨማሪም በጥቂት የቄለም ወለጋ እና ሸካ ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

.Tomorrow the forecast indicates that favorable weather conditions for rain will continue to prevail in the main areas of the country that receive the belg rains, as well as in the western and northwestern regions of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and South West Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; In all zones of Sidama Region; Dawa, Liben, Fafen, Nogob, Jarar, Dolo, Korahe and Erer zones from Somali Region; Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones from Southwestern Ethiopia Region; Majang, Nuer, Agnuak and Itang zones from Gambella Region; Metekal, Kamash, Asosa and Maokomo zones from Benishangul Gumuz Region; The West and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of Amhara region and the Central Zone of Tigray region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities. In addition, a few areas of Kelem Wellega and Sheka will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours.