Daily Weather Report 26 April 01

Weather Summary for previous day

March 31, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ደቡብና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ፣ ዲመካ፣ ቀርሳ እና ጎሮበቀርሳ ከ30-56.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በማይሃንሳ፣ አዲስ ዘመን፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጨለንቆ፣ መንደር 11፣ ሰመራ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

There were cloud cover in the western and central regions of the country that benefited from the belg rains yesterday. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, East, Southwest and North Shewa, Hawassa, Ilubabor, East Wellega, East Gojam, North and South Wollo and South and East Tigray; Addis Ababa, Dimeka, Kersa and Gorobekersa received heavy rainfall of 30-56.8 mm. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Mayhansa, Addis Zemen, Gewane, Awash Arba, Metahara, Chelenko, Village 11, Semera and Elidar.

Weather Forecast for next day

April 2, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ፋፈን፣ኖጎብ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

Tomorrow, there will be cloud cover over the main areas of the country that benefit from the belg rains, as well as over the western and northwestern regions of our country. In addition, there will be cloud cover over the Oromia Region, including Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem and West Wellega, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all Sidama Region zones; from the Somali Region, Dawa, Liben, Fafen, Nogob, Jarar and Erer zones; from the Southwestern Ethiopia Region, Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones; From the Gambella region, Majang, Agnewak and Itang zones; The Metekel, Asosa and Maokomo zones of Benishangul Gumuz region; the West and East Gojam, Central and South Gondar, North and South Wollo zones of Amhara region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many areas. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities.