Daily Weather Report 25 September 29

Weather Summary for previous day

Sept. 28, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአይራ፣ ነቀምቴ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ አድርቃይ፣ ሐሮ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefited from the kiremt rains. In connection with this, many of them received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Aira, Nekemte, Kidame Gebeya, Adrakay, Haro and Addis Ababa within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 30, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌእና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቤጊ፣ ጊዳሜ፣ አንፊሎ፣ ሳሲጋ፣ ነቀምቴ፣ ሊሙ ሰቃ፣ ቀርሳ፣ በኔሳ፣ ቦና ዙርያ እና አሮሬሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremet rains. Therefore, the western and northwestern zones of Tigray region; the western, northern, southern and central Gondar of Amhara region; North, West and East Gojam and Awi zones; from Benishangul Gumuz region, Metekel, Asosa, Kamash and Maokomo zones; from Oromia region, Jima, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horogudru, West and East Wollega, North, West, South-West and East Shewa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; From Gambella Region: Majang, Itang, Nuer and Agnuak Zones; From Southwestern Ethiopia Region: Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta Zones; From Central Ethiopia Region: Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; From Southern Ethiopia Region: Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, Kore and Gedio Zones; Sidama Region zones and Fafen, Erer, Jarar and Dolo zones of Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Begi, Gidame, Anfilo, Sasiga, Nekemte, Limu Seka, Kersa, Benesa, Bona Zuria and Aroresa will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours, our numerical forecast data indicates.