Daily Weather Report 25 September 26

Weather Summary for previous day

Sept. 25, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፓዌ፣ ዳንግላ፣ ጊምቢ፣ ዪና እና አዲስ ዘመን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western half, northeastern, central, eastern and southern parts of our country had cloud cover. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in many places. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Pawe, Dangla, Gimbi, Yina and Addis Zemen in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 27, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጉባ፣ ዳንጉር፣ ማንዱራ፣ ቡለን፣ ወንበራ፣ ቻግኒ፣ አየሁ፣ ዳንግላ፣ ሰከላ፣ ፍኖተሰላም፣ ቡሬ፣ ደምበጫ፣ ኢባንቱ፣ በደሌ ዙርያ፣ መኮ፣ ሰተማ፣ ቦረቻ፣ ደዴሳ እና መቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow there will be strong cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremet rains. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; the North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam and Awi zones; from Oromia Region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, East, Kelem and Horogudru Welge, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from Gambella Region, Itang, Nuer, Agnua and Majang zones; ; From Benishangul Gumuz Region, Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; From Southwestern Ethiopia Region, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; From Central Ethiopia Region, Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Marekko Special Zone, Mem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; Sidama Region Zones, The Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Kore, Gardula and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region and the Siti and Fafen zones of the Somali Region will experience light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Guba, Dangur, Mandura, Bulen, Wenerbera, Chagni, Ayehu, Dangla, Sekela, Fnoteselaam, Bure, Dembecha, Ibantu, Bedele Zuria, Meko, Setema, Borecha, Dedesa and Metu will experience heavy rainfall of more than 30mm within 24 hours.