Daily Weather Report 25 September 25

Weather Summary for previous day

Sept. 24, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአድዋ፣ ካቺሴ፣ አዋሽ አርባ፣ ቁሉቢ፣ ኩርፋጨሌ፣ ባቱ እና ኦቦመርጋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefited from the Kiremt rains. In connection with this, many of them received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, heavy rain of more than 30 mm was recorded in Adwa, Kachise, Awash Arba, Kulubi, Kurfachele, Batu, and Obomerga in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 26, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በደቡብ አቸፈር፣ ዳንግላ፣ አዲስ ቅዳም፣ ቻግኒ፣ ሰከላ፣ ደምበጫ፣ ፍኖተ ሰላም፣ መናሲቡ፣ መንዲ፣ ጃርሶ፣ አይራ፣ ጉሊሶ፣ ሳሲጋ፣ ሊሙ፣ ግንደበረት፣ ኢሉ ገላን፣ ሊበን ጃዊ፣ አዳአባርጋ እና አምቦ ዙሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Weather conditions that are conducive to rain will continue in the same manner tomorrow.

Tomorrow, weather conditions that are conducive to rain will continue in the same manner. In this regard, the western, central and north-western zones of Tigray region; From the Amhara region, the North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi and North Shewa zones; from the Oromia region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelam and Horogudru Wellega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang and Agnuwak zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burji, Konso and Gedeo zones of Southern Ethiopia Region and Siti and Fafen zones of Somali Region will experience light to moderate rainfall in many areas. Additionally, based on the intensifying weather events, our numerical forecast data indicates that heavy rainfall of more than 30 mm will occur in the southern regions of Achefer, Dangla, Addis Qedam, Chagni, Sekela, Dembecha, Finote Selam, Mena Sibu, Mendi, Jarso, Aira, Guliso, Sasiga, Limmu, Gindeberet, Ilu Gelan, Liben Jawi, Adaberga, and Ambo within 24 hours.