Daily Weather Report 25 September 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንጋር ጉቴ ፣ ቻግኒ እና አቦምሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday many parts of our country that benefit from Kiremt rains were cloudy and misty. In several places they recorded light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, Angar Gute, Chagni and Abomsa received heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ ፤ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ ዞን እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዲባጥ፣ ካማሺ፣ኢባንቱ፣ሃሮ ቡሉክ፣ ሀሮ ሊሙ፣ ጉዱሩ፣አቤ ዶንጎሮ፣ ሳሲጋ፣ ዲጋ፣ ጉቶ ጊዳ፣ ባኮ ቲቤ፣ ኢሉ ጋላነ፣ጊዳ ኣያና፣አስገደ፣ፅምብላ፣ ጸለምቲ ፣ሊሙ ፣ጂማ ራሬ ፣ሚዳ ኬኝ ፣ጫሊያ ፣ጂማ አርጆ፣ ዋማ ሀጋሎ፣ ኖኖ ኩመባ፣ በደሌ ዙሪያ፣ ጌቺ እና ሌቃ ዱላቻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, in areas of the country that benefit from the winter rains, there will be heavy cloud cover with mist and drizzle. In addition, light to moderate rain is expected in many places across the following zones: from Tigray Central, Northwestern and Western zones; from Amhara North, West, South and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi, South Wollo, North Shewa and Wag Hemra zones; from Oromia Jimma, Illubabor, Buno Bedele, West, East, Kellem and Horo Guduru Wellega, West, Southwest, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, East and West Hararghe, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; also Addis Ababa, Dire Dawa and Harar; from Gambela Itang, Nuer, Agnuak and Majang zones; from Benishangul Gumuz Assosa, Mao Komo, Kamashi and Metekel zones; from Southern west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta and Dawuro zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Kebena and special zones, Mareko special zone, Me special zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones; Sidama zones; from Southern Ethiopia Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Afar Gabi zone; from Somali Sitti and Fafan zones light to moderate rain is expected. Furthermore, due to strengthening of weather conditions, over places such as Dibati, Kamashi, Ibantu, Haro Buluk, Haro Limu, Guduru, Abe Dongoro, Sasiga, Diga, Guto Gida, Bako Tibe, Ilu Galan, Gida Ayana, Asgede, Tsimbla, Tselemti, Limu, Jima Rare, Mida Kegn, Chaliya, Jima Arjo, Wama Hagalo, Nono Kumba,Bedele Zuria,Gechi and Leka Dulacha will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours.