Daily Weather Report 25 September 23

Weather Summary for previous day

Sept. 22, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ፣ ላንጌ፣ አቦመርጋ እና ወራቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover and precipitation in the mid-west, central, northeast, east, and southern regions of our country. Consequently, many areas received light to moderate (1 to 29 mm) amount of rainfall. Additionally, more than 30 mm of heavy rainfall were recorded in Chagni, Lange, Obomerga, and Werabe in a 24-hour period.

Weather Forecast for next day

Sept. 24, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአብርሀሞ፣ ባምባሲ፣ ማኦኮሞ፣ ካማሽ፣ ማናሲቡ፣ ቤጊ፣ ሳዮ፣ ሳሲጋ፣ ዲጋ፣ አርጆ፣ ጉቡሳዮ፣ ኖኖቤንጃ፣ ሊሙሰቃ፣ ቦርቻ፣ ደዴሳ፣ ጨዋቃ፣ መኮ፣ ሰተማ፣ ሳይልማ፣ ማሻ፣ ኮራን እና ቤንሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be cloudy cover across the Kiremt rain benefiting areas of our country. Thus, the central, northwest and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; from Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; Sidama region zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio and Basketo zones and from Somali region Fafen, Siti and Jarrar zones will receive light to moderate amount of rain. In addition, in Abraham, Bambasi, Maokomo, Kamash, Mana Sibu, Begi, Sayo, Sasiga, Diga, Arjo, Gobuseyo, Nonobenja, Limuseka, Borcha, Dedessa, Chewaka, Meko, Setema, Sailma, Masha, Koran, and Benas are expected to experience heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour period.