Daily Weather Report 25 September 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ፣ በምዕራብና መካከለኛው አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ምዕራብ መካከለኛው እና ምስራቅ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጊዳአያና፣ ካቺስ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ አማን፣ ሙጊ እና የሪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, Central, Eastern and Southern Tigray, Western and Central Amhara, Benshangul Gumuz, Western Central and Eastern Oromia, Central Ethiopia, Gambella, Southwestern Ethiopia and Sidama experienced cloud cover and accumulation. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was observed in many places. Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Gidaayana, Kachis, Gore, Chira, Aman, Mugi and Yeri within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በባህርዳር፣ ጉሊሶ፣ ላሎቂሌ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ መኮ፣ ያዮ፣ ጮራ፣ ሰተማ፣ አጋሮ፣ ሊሙ ኮሳ፣ ሊሙ ሰቃ እና ቀርሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions conducive to rain will continue to prevail. In this regard, the western, central and northwestern zones of Tigray region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Majang and Agnwak zones from Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardolla, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones of Southern Ethiopia Region; Awsi, Hari and Fanti zones of Afar Region and Siti and Fafen zones of Somali Region will receive light to moderate rainfall in many areas. Additionally, our numerical forecast data indicates that Bahir Dar, Giulios, Lalukile, Gimbi, Chewaka, Meko, Yayo, Chora, Setema, Agaro, Limu Kosa, Limu Seka, and Kersa will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours, based on the intensifying weather events.