Daily Weather Report 25 September 19

Weather Summary for previous day

Sept. 18, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቁልቢ፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ መተከል፣ በደሌ፣ አባይሸለቆ፣ ቡልቡል፣ ሐሮ እና ያንፋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefited from the kiremet rains. In connection with this, many places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Kulubi, Bahir Dar, Debre Tabor, Metekel, Bedele, Abay Shelleko, Bulbul, Haro and Yanfa within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 20, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ ይጠናከራሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በዳንሻ፣ ፀገዴ፣ ታህታይ አድያቦ፣ ደባርቅ፣ ጃናሞራ፣ መተማ፣ አይከል፣ ጎንደር፣ እብናት፣ አዲስ ዘመን፣ ወረታ፣ ፎገራ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ነፋስ መውጫ፣ እነማይ፣ ደጀን፣ ቢቸና፣ ሸበል በረንታ፣ ጫንጮ. ሱሉልታ፣ ኢልፈታ፣ አምቦ ዙርያ፣ ሊበን ጃዊ፣ ወንጪ፣ ወሊሶ፣ አረርቲ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ በደሌ፣ ጉና፣ ጎሎልቻ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions conducive to the occurrence of kiremt rains will intensify. In this regard, the Central, North-West, South-East, South and East zones of Tigray Region; the North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones of Amhara Region; the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South-West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi zones of Oromia Region; the West and East Hararge, Borena, Bale, Guji and West Guji zones of Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; From Benishangul Gumuz Region: Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel Zones; From Gambella Region: Majang, Itang, Nuer and Agnwak Zones; From Southwestern Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro Zones; From Central Ethiopia Region: Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Mem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro Zones; From Sidama Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardolla, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio Zones; Gabi, Hari and Fanti zones of Afar region and Siti and Fafen zones of Somali region will receive light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Dansha, Tsegde, Tahtai Adiabo, Debarq, Janamora, Metema, Aikel, Gondar, Ebnat, Addis Zemen, Wereta, Fogera, Mekane Yesus, Neifs Ntul, Enmay, Dejen, Bichena, Shebel Berenta, Encho. Sululta, Ilfata, Ambo Zuria, Liben Jawi, Wenchi, Wolisso, Areti, Mojo, Adama, Bedele, Guna, Gololcha and Addis Ababa will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours, our numerical forecast indicates.