Daily Weather Report 25 September 18

Weather Summary for previous day

Sept. 17, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአትናጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

yesterday Cloud cover and accumulation were observed in the areas of our country that benefited from the kiremt rains. In connection with this, many areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall, with heavy rainfall of more than 30 mm recorded in Atango in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 19, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፈንቲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በወልቃይት፣ ሽሬእናዳስላሴ፣ አድዋ፣ የጭላ፣ አክሱም፣ መተማ፣ አይከል፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ በለሳ፣ እብናት፣ አዲስ ዘመን፣ ወረታ፣ ፎገራ፣ ኩታበር፣ መቅደላ፣ አቅስታ፣ ላጋምቦ፣ ደብረብርሃን፣ ሊሙ ኮሳ፣ ደዴሳ፣ ጮራ፣ ኢልፈታ እና በአምቦ ዙርያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of kiremt rains will be stronger. Therefore, the West, Central, North-West, South-East and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, the western, northern, southern and central Gondar, northern, western and eastern Gojam, Awi zone, northern Shewa and Waghemra zones; from the Benishangul Gumuz region, the Metekel, Asosa, Kamash and Maokomo zones; from the Oromia region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horogudru, western and eastern Wollega, northern, western, southwestern and eastern Shewa, Arsi and western Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Hararge zones; Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones from Afar region; Addis Ababa; Majang, Nuer, Itang and Agnewak zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem special Zone, Kembata and Tembaro Zones from Central Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, Kore and Gedio Zones of the Southern Ethiopian Region; Sidama Region Zones and Fafen Zone of the Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Welkait, Shireendesilase, Adwa, Yechila, Axum, Metema, Aykel, Debark, Dabat, Gondar, West and East Balsa, Our numerical forecast data indicates that Ebnat, Addis Zemen, Wereta, Fogera, Kutaber, Mekdela, Akesta, Legambo, Debre Berhan, Limu Kosa, Dedesa, Chora, Ilfeta and the surrounding areas of Ambo will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.