Daily Weather Report 25 September 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በመተማ፣ አይራ፣ አንገርጉትን፣ ጎሬ፣ ሀሮ እና ያዮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation across the western half, central, eastern, and southern parts of our country. In association with this, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in many places. Additionally, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Metema, Aira, Angergutin, Gore, Haro, and Yao within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተመሳሳይ መልኩ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጭልጋ፣ ደራ፣ ደቡብ አቸፈር፣ ሁለትእጅነሴ፣ ዳንጉር፣ ቡለን፣ መንገሽ፣ ኢባንቱ፣ ሊሙ፣ አርጆ፣ ኑኑኩምባ፣ አቤዶንጎሮ፣ ባኮጢቤ፣ ዳኖ እና ኖኖ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, Weather conditions favorable to the formation of rain will continue in similar manner. Thus, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; Sidama region zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Burji, south Omo and Basketo zones and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate amount of rain. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours in Chilga, Dera, South Achefer, HuletEjnese, Dangur, Bullen, Mengeshi, Ibantu, Limu, Arjo, Nuno Kumbi, Abe Dongro, Bakotibe, Dano, and Nono.