Daily Weather Report 25 September 15

Weather Summary for previous day

Sept. 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ እና ምዕራብ አማራ፣ በምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ እና በሲዳማ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሸርኮሌ፣ አርባምንጭ፣ ሐሮ፣ ያንፋ፣ ጎሎልቻ እና ጎሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in East and West Amhara, West, Central, East and South Oromia, Central Ethiopia, South Ethiopia, Gambella and Sidama. In connection with this, many places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Sherkole, Arbaminch, Haro, Yanfa, Gololcha, and Goro within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 16, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሃገረ ሰላም፣ ወንበራ፣ ቡለን፣ ድባጢ፣ ግምጃቤት፣ ቲሊሊ፣ ቡሬ፣ ደምበጫ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባሶ ሊበን፣ ኢባንቱ፣ ሀሮ ሊሙ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ጉድሩ፣ ሊሙ ሰቃ፣ ሊሙ ኮሳ፣ ጮራ፣ አሮሬሳ እና በኔሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation in the areas of our country that benefit from kiremt rains. Therefore, the West, Central, North West, South East and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, the western, northern, southern and central Gondar, northern, western and eastern Gojam, Awi zone, northern Shewa and Waghemra zones; from the Benishangul Gumuz region, the Metekel, Asosa, Kamash and Maokomo zones; from the Oromia region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horogudru, western and eastern Wellega, northern, western, southwestern and eastern Shewa zones; Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Majang and Anuak zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; The Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, Kore and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region; Sidama Region zones and the Fafen zone of the Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Hagere Selam, Wenerbera, Bulen, Dibate, Gmjabet, Tili, Bure, Dembecha, Debre Markos, Basso Liben, Ibantu, Haro Limu, Gidayana, Shambu, Gudru, Limu Seka, Limu Kosa, Chora, Aroresa and Benesa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.